1 month agoETB Aበዶክተር ሰላማዊት ታደሰ የተደረሰውና በታሪካዊ ሁነት ላይ የተንተራሰው በንጉስ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የውጪ ጉዳይ ሚንስትር በነበሩት አክሊሉ ሐብተወልድ ላይ የሚያተኩረው " አክሊሉ " የተሰኘው ታሪካዊ የልቤለድ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል !!
1 month agoETB Aከምድራችን ውጪ የሚገኙ ፍጥረታት በምድራችን ላይ በዘረጉት ረጅምና ጥልቅ የማጥመጃ መረብ በተለይ የፋሽን፣ የኮስሞቲክስ ኢንዱስትሪና የመዝናኛ አውታሮችን በመጠቀም ግብረ ሰዶማዊነትን በስፋት በማስተዋወቅና ይህ እርኩሰት የሰው ልጆች የነፃነትና የመብት ጉዳይ እንደሆነ በሰዎች አእምሮ ለማስረጽ በኢኮኖሚና በፖለቲካ የፈረጠሙ ሀያላን ሀገራትን በመጠቀም በመላው አለም የእርኩሰት ልምምዱን በማበረታታት እንዲስፋፋ በማድረግ ላይ ናቸው። በዚህም የሰው ልጅ በእግዚአብሄር ላይ እንዲያምጽ ከግለሰቦችና ከመንግስታት በላይ አቅም ባላቸው በፈረጠሙና በፍጥረታቱ አለፍ ሲልም ከሰው ልጆች ጋር በማዳቀል በተፈጠሩ ፍጥረታት ቀጥተኛ ቁጥጥር በሚደረግባቸው ዘርፈ ብዙና የአለምን ኢኮኖሚ በተቆጣጠሩባቸው ተቋማት አማካኝነት በብርቱ የተፅዕኖ በትራቸውን በማሳረፍ ላይ ይገኛሉ። ከምድራችን ውጪ የተለያየ ዝርያ ያላቸው ፍጡራን መነሻቸው ከሰማይ የወረዱ መላዕክት እንደሆኑና እነዚህም መላዕክት ከሰው ዘር ጋር በተለያየ መንገድ በማዳቀልና የተለዩ ዝርያዎችን በመፍጠር በምድራችን ውስጥም ሆነ ከምድራችን ውጪ መኖሪያቸውን እንዳደረጉና በመሪያቸው ሉሲፈር እየተመሩ በመሰረታዊነት ዲያቢሎስ በምድር ላይ ሊያሳካ የሚፈልገውን አላማ ለመፈፀም በመስራት ላይ የሚገኙ ናቸው።
1 month agoETB Aበዓለማችን ውስጥ ከሚገኙት ቀዳሚ ስልጡን ሀገራት መካከል አንዷ ነኝ ብላ የምታስበው ግብፅ በራሷ ፍላጎት ብቻ በመመራት የዓባይን ውሃ እስከ ዛሬ ድረስ እያቆረች በመጥለፍ ትጠቀማለች። ከበርካታ መቶ ዓመታቶች በላይ ለሚሆን ጊዜ ግብፆቹ በዓባይ ውሃ ሀብት ላይ ተፈጥሯዊና ታሪካዊ የሆነ የመጠቀም መብት አለን በማለት ሲከራከሩ ኖረዋል። ይሄው የይገባኛል ሙግታቸው ነው እንግዲህ በዓባይ ውሃ ክፍፍልና አጠቃቀም ረገድ ዛሬ ላይ ግብፅን ከላይኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ውዝግብ ውስጥ የከተታት። በላይኛው የተፋሰሱ መልከዓ-ምድር የሚገኙት የዓባይ ወንዝ ባለድርሻ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ነፃ ከወጡ በኃላ ዓባይንና ገባሮቹን የመጠቀም ፍላጎታቸው ብቻ ሳይሆን አቅማቸውም ጭምር እየጎለበተ መምጣቱን መረዳት ከባድ አይሆንም። የላይኛው ተፋሰስ ባለድርሻ ሀገራት ዓባይን የመጠቀም ፍላጎትና አቅም እየጨመረ መምጣት ደግሞ በግብፃውያኑ ባለስልጣናት ዘንድ ክስተቱ በግብፅ ዜጎች ላይ እንደተቃጣ ብሔራዊ የህልውና ስጋት ተደርጎ መወሰዱን እያየን ነው። በተለይ ከቅኝ አገዛዝ እሪሷን ተከላክላ በነፃነት የኖረችው ኢትዮጵያ በዓባይ ውሃ ዙሪያ የምታደርጋቸው የልማት እንቅስቃሴዎች በግብፃውያኑ ዘንድ እንደ አደገኛ የህልውና ስጋት ተደርጎ ነው የተወሰደው።..
1 month agoETB A°°° ደግሞ እንደ ገና በእግዚአብሔር ቸርነት በሦስተኛ የልብ ወለድ ድርሰት ተመልሰናል። ምስጋናው የቤተሰብ፥ የወዳጅ እና የእናንተ የአንባቢያን ነው። «ጠይም ፡ ትውስታዎች» ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ (ሰኔ 11) በጃዕፈር መጻሕፍት አሳታሚና አከፋፋይ በኩል በገበያ ላይ ይውላል።
1 month agoETB A"የዝሆኖች ፀብ ሳሩን ይጎዳል። አሳዛኙ እውነት የዝሆኖች ፍቅርም ሳሩን መጉዳቱ ነው። ዝሆኖች በፀብ ሲፋለሙም ሆነ በፍቅር ሲላፉ ሳሩ መከራ ይወርድበታል። ከታችኛው መደብ ያለ ዘወትር ይረገጣል" ይላሉ መብራታዊያን። "የዝሆኖች የፀብ ፍልሚያ ሆነ የፍቅር ልፊያ ሳሩን ያደቀዋል። መላው ገደል መሆን ነው። ሳር ከመሆን ይልቅ ገደል መሆንን የሚመርጥ ብልህ ነው። ገደሉ በልፊያ እና በፍልሚያ ደክመው የሚረግጡትን ያስወግዳል። አክሳሚውን ያከስማል" ይላሉ የመብራት አዛውንቶች። መብራታውያን ማህበረሰባቸውን ሲያዋቅሩ ማህበራዊ ደረጃን አበጅተዋል። የሸንጎው ጉባዔ በምድራዊ ስልጣን አናት ላይ ይገኛል። ከሸንጎው ጉባዔ በላይ ያለው የእምዬ መብራት "ቅዱስ" መንፈስ ነው። ከመብራት መንፈስ በላይ ፈጣሪ አለ።
1 month agoETB 4“ካራሞን” ዋኖስ እና ጭልፊት በአዛሪስ ደሴ አሁን በመደብራችን ያገኙታል https://vt.tiktok.com/ZSQ8V2fns/ 📍4Killo ብርሀን እና ሰላም ማተምያ ፊት ለፊት 📍መገናኛ መሠረት ደፋር ህንፃ ስር 📍Mexico ደብረወርቅ ህንፃ ንግድ ባንክ አጠገብ 📍ጀሞ ሚካኤል መብራቱ ጋር ሚናሞል ፊት ለፊት 📍4Killo አብርሆት ግቢ ውስጥ 📍ለገሀር ኖክ ማደያ ጎን 📍በተጨማሪም ስድስት ኪሎ ዩንቨርስቲ እየተካሄደ ባለዉ የመፀሀፍ ዐዉደ ርዕይ ጃዕፋር መፀሀፍት ጋር ያገኙታል
1 month agoETB Aበአጎራባቿ ሠራባ ከተማ ምዕራብ በኩል መቶ ሜትር ወጣ ብዬ ዋልድባ ጫፍ ላይ ቆሜያለሁ። ረፋድ ሆኖል። መምህሩ አሁንም አጠገቤ ድንዛዜዬ ያስጨነቀው መስሎ በጸጥታ ተገትሯል። ሠራባ ልክ እነደ እረኛ ጋሜ የተራራ ጫፍ ላይ ጉች ያለች እንደነገሩ ከተማ ነች። ከጀርባዬ አንድ ክፍለ ጦር የወታደር ካምፕ ሰፎሯል። ከአዲስ አበባ ካርቱም የሚዘልቀው መንገድ ከተማዋን ለሁለት ከፍሎ የወታደር ካምፑን ወደ ግራ ትቶ ወደ እልፍ ይጉዳል። ማየት እስከምችለው ጥግ መንገዱን ተከተልኩት። ዓይኖቼን እያንከራተትኩ ዙሪያ ገባውን ለመቃኘት ሞከርኩ እዚያ ማዶ በሰሜን በኩል አይደፈሬዎቹ የወልቃይት ምድር ሰልፈኛ ተራሮች ስትር ብለዋል። አሰላለፋቸው የሆነ ተጠንቀቅ ነገር አለበት። በላያቸው ላይ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገረ ሰጋር የበልግ ንፋስ በማናለብኝነት ይጋልባል። በግራዬ በኩል እስከ አድማሱ ጥግ ተንጣሎ የሚታየኝ የቋራ ምድር ነው።በመካከል የዮሐንሱ መተማ አርምሞን ተከናንቦ ተዘርግቷል። መምህሩ ሹክክ ብሎ ተጠግቶኝ አለኝ... "ሆይ ሆይ... እመትዋ ሠራባን መቶ ሜትር አልፈው ዋልድባን ተረገጡ ማቆልቆል ነው።" አዎ መተማን፣ ካርቱምን፣ ሱዳንን፣ ካይሮን፣ ምናልባት ባቢሎልንን ኹሉ አልፎ የሚሄድ ዘላለም የሚመስል ቁልቁለት የሚጀምረው እዚህ ጋር ነው።...